በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

11/03/2025

Financial and Audit Report 2020/21

28/01/2025

ማስታወቂያ

25/10/2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ

26/12/2024

የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ

02/12/2024

ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ

23/10/2024

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

23/10/2024

በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ

14/10/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!!

11/10/2024

ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ

26/08/2024

ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ

22/07/2024

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ

20/07/2024

የማዕከላዊና የምዕራብ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና 2017 የኮርፖሬት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ

20/05/2024

ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ

13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 50 results.

ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎች ለመሸለም ሐምሌ 14 ቀን 2016 . በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል በተዘጋጀው የእውቅና ስነ ስርዓት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ፡፡

በዝግጅቱ የዕለቱ የክብር እንግዳ፣ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንትና የአቢሲኒያ ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ / ሙላቱ ተሾመ ሽልማቱን ሰጥተዋል፡፡

ሽልማቱን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ / የሺመቤት ነጋሽ የተረከቡ ሲሆን ድርጅቱ በኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ለዓመታት በሰጠው አገልግሎት እንዲሁም ጥራትንና ደንበኞችን ማዕከል በማድረግ ላከናወናቸው ተግባራት ሽልማቱ እንደተሰጠው ተገልጿል፡፡

በሽልማቱ ሥነ ስርዓት ላይ የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ በሰጡት ጠንካራ አመራር የወርቅ ሜዳልያ፣ ኒሻንና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተያያዘም 12 መካከለኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ሜዳልያና ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን እንደተቋም በወርቅ ደረጃ ድርጅቱ ዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት 33 ኢንዱስትሪዎች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎች እንዲሁም ድርጅቶቹን ለዚህ ያበቁ አመራሮችና ባለሙያዎቻቸው ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ደርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በመግዛት ማቅረብና በሂደትም በአገር ውስጥና በውጭ አገር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ለማቅረብ የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡